የመብራት ኃይል ሠራተኞች ነን በሚል ከፍተኛ ትራንስፎርመር በክሬን የጫኑ ግለሰቦችን እጅ ከፍንጅ መያዙን ፖሊስ አስታወቀ

ግለሰቦቹ በኃላፊያቸው ታዘው ትራንስፎርመር ለመቀየር መምጣታቸውን ቢናገሩም በኢትዮጲያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፖሬሽን የምስራቅ አዲስ አበባ ዲስትሪክት የኮንስትራክሽንና ሜንቴናንስ ኃላፊ አቶ ሱልጣን ሰርሞሎ ግለሰቦቹን መሥሪያ ቤቱ እንደማያውቃቸውና ከመሥሪያ ቤቱ የታዘዙ ቢሆኑ እንኳን የትዕዛዝ ደብዳቤ መያዝ እንደነበረባቸው ገልፀዋል።

ለማነኛውም ትዕዛዝ ሰጥቶናል እንድንሰራ ያሉትንም ሓላፊ ከፖሊስ ጋር በጋራ እንደሚያጣሩት በበኩላቸው አስረድተዋል።

ፖሊስ የምርመራ ሂደቱን ለመቀጠል ተጠርጣሪዎቹንና በእግዚቢትነት የተያዙ ንብረቶችን በቁጥጥር አውሎ ምርመራ መጀመሩን የገለጹት ኮማንደር ያሲን ሁሴን፥ በመብራትና በሌሎች የመሰረተ ልማት አውታሮች ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎችን ለመከላከል ህብረተሰቡ ከፖሊስ ጋር በመቀናጀት አካባቢውን መጠበቅ እንዳለበት ጥጭሪ አቅርበዋል።

የመብራት ኃይል ሰራተኞች ነን በሚል የሚመጡ ግለሰቦች ሲያጋጥሙት ህጋዊ ሰራተኞች ስለመሆናች በአግባቡ ማረጋገጥ ይኖርበታል ሲሉ ኃላፊው መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።


የመብራት ኃይል ሠራተኞች ነን በሚል ከፍተኛ ትራንስፎርመር በክሬን የጫኑ ግለሰቦችን እጅ ከፍንጅ መያዙን ፖሊስ አስታወቀ