ባለፉት 24 ሰዓታት 915 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ሲገኝባቸው የ11 ሰዎች ህይወት አልፏል

በአሁኑ ወቅት 138 ፅኑ ታማሚዎች የሚገኙ ሲሆን 187 ሰዎች ደግሞ ከቫይረሱ አገግመዋል።

ይህን ተከትሎም ከቫይረሱ ያገገሙት ሰዎች ቁጥር 6 ሺህ 950 እንደደረሰም ነው ሚኒስትሯ ያስታወቁት።

እንዲሁም በ24 ሰዓታት በኮሮና ቫይረስ ምክንያት የ11 ሰዎች ህይወት አልፏል፡፡

በኢትዮጵያ እስካሁን በቫይረሱ ምክንያት 274 ሰዎች ህይወታቸውን አጥተዋል።

በአጠቃላይ ለ422ሺህ 354 ሰዎች የላቦራቶሪ ምርመራ መደረጉንም አስታውቀዋል፡፡


ባለፉት 24 ሰዓታት 915 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ሲገኝባቸው የ11 ሰዎች ህይወት አልፏል