ሆንግ ኮንግ ምርጫዋን አራዘመች

ምርጫውም ለአንድ ዓመት መራዘሙ ነው የተነገረው፡፡

የምርጫውን መራዘም ተከትሎም ተቃዋሚ ፓርቲ መንግሥት ወረርሽኙን እንደ ምክንያት በመጠቀም ሕዝቡ የሚፈልገውን እንዳይመርጥ እያደረገ ሲሉም ከሰዋል ነው የተባለው፡፡

የሆንግ ኮንግ ዋና አስተዳዳሪ ካሪ ላም የምርጫውን ጊዜ ለማራዘም የአስቸኳይ ጊዜ የማወጅ ሥልጣናቸውን ሊጠቀሙ እንደሚችሉ አስታውቀው÷ባለፉት ሰባት ወራት ውስጥ ከሰጠሁት ውሳኔዎች ሁሉ ይህ እጅጉን አስቸጋሪ ውሳኔ ነው ብለዋል።

በሃገሪቱ የኮሮና ቫይረስ እየተስፋፋ ሲሆን በ24 ሰዓት ውስጥም 121 ሰዎች በቫረሱ ተይዘዋል፡፡

በአጠቃላም በግዛቷ 3ሺህ273 ሰዎች በቫይረሱ ሲያዙ 27 ሰዎች ለህልፈት ተዳርገዋል፡፡

ምንጭ፡-ቢቢሲ


ሆንግ ኮንግ ምርጫዋን አራዘመች