በኢትዮ-ሱዳን ድንበር ታሪካዊ ዳራ ላይ ያተኮረ መድረክ በጎንደር እየተካሄደ ነው

የምዕራብ ጎንደር ዞን አስተዳደር አቶ አደባባይ ሙሉጌታ በበኩላቸው በሁለቱ ሃገራት ረጅም ዓመት ያስቆጠረ የሰላም ግንኙነት እንዳላቸው አንስተዋል፡፡

ከዚህ ባሻገር ደግሞ አልፎ አልፎ በሃገራቱ ድንበር ላይ የሚነሱ ግጭቶች ጥቁር አሻራ ጥሎ አልፏል ብለዋል፡፡

በውይይቱ ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት የአማራ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ ተመስገን ጥሩነህ በንግግራቸው በሁለቱ ህዝቦች መካከል ቅራኔ እና ቁርሾ የለም ለወደፊትም አይኖርም ብለዋል፡፡

የሚነሱ ችግሮችን በሰላማዊ መንገድ መፍታት ይቻል ዘንድ በምሁራን መደገፍ አስፈላጊ መሆኑን አንስተው፥ ይህ ውይይት የመጨረሻ ሳይሆን ለወደፊትም መሰል ውይይቶች ይቀጥላሉ ብለዋል፡፡

በኤሊያስ አንሙት


በኢትዮ-ሱዳን ድንበር ታሪካዊ ዳራ ላይ ያተኮረ መድረክ በጎንደር እየተካሄደ ነው