ኦሮሚያን አቋርጠው የሚያልፉ የከባድ ጭነት ተሽከርካሪዎች ፈተና

ከቅርብ ወራት ወዲህ ከአማራ ክልል በደጀን መስመር ወደ አዲስ አባባ የሚሄዱና የሚመለሱ ከባድ የደረቅ የጭነት ተሸከርካሪ አሽከርካሪዎች በተለይ በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ከጎሐጽዮን ደብረጉራቻ ባለው መስመር ማለፍ ፈተና ሆኖባቸዋል።

አስተያየታቸውን ከሰጡት አሽከርካሪዎች መካከል አንዱ ”ከፍቼ ከተማ የቅርብ ርቀት ከምትገኝ ‘አሊ ዶሮ’ ከተባለች ቦታ ላይ መስከረም 30/2013 ዓ. ም የክልሉን የፀጥታ ኃይሎች የደንብ ልብስ የለበሱ ታጣቂዎች ተኩስ ከፍተው የቆሰሉና ከፍተኛ ጉዳት የደረሰባቸው አሽከርካሪዎችና ከ10 በላይ የተሰባበሩና የተቃጠሉ መኪናዎች አሉ” ብሏል።

እየደረሰ ያለውን ጉዳት በዝርዝር ያስረዳው ይኸው አስተያት ሰጪ፣ በአሽከርካሪዎችና በንብረት ላይ የደረሰውን ጉዳት በተመለከተ  ሰሞኑን እስከ 70ና 80 የሚሆኑ አሽከርካሪዎች ከነተሸከርካሪዎቻቸው ለአማራ ክልል የተለያዩ ባለስልጣናት አቤቱታ ማቅረባቸውን ገልጧል።

የአማራ ክልል የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ዋና ዳይሬክተር አቶ ግዛቸው ሙሉነህ የተገደለ አሽከርካሪና የወደመ ንብረት መኖሩን ጠቁመው ከጥቃቱ ጀርባ ማን አለ የሚለው ግን የኦሮሚያ ክልል የሚያጣራው ይሆናል ብለዋል።

“ችግር ስለመፈጠሩ አላውቅም” የሚለው የሰሜን ሸዋ ዞን አስተዳደርና ፀጥታ ምላሽ ግን መሰረት የለውም ያሉት ዳይሬክተሩ፣ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት የችግሩን ፈጣሪዎች ለማደን ከፍተኛ ጥረት እያደረገ እንደሆነ ተናግረዋል። ችግሮችን ለመፍታት በጋራ እንደሚሰራ ዳይሬክተሩ አረጋግጠዋል።

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ

Print Friendly, PDF & Email

Source Article from https://www.goolgule.com/heavy-duty-trucks-denied-access-to-pass-oromia/


ኦሮሚያን አቋርጠው የሚያልፉ የከባድ ጭነት ተሽከርካሪዎች ፈተና