እናንተ እውነትን የምትደባብቁ ነግ በኔ በሉ! ! (አሌክስ አብርሃም)

ebc-liesኢቢሲ “በቀኑ ዜና እወጃየ በጎንደር ማረሚያ ቤት ትላንት በደረሰው የእሳት ቃጠሎ የሞተ ሰው የለም ብየ የዘገብኩት ኮማንደር ሰይድ ሃሰን የሚባሉ የማረሚያ ቤቱ ሃላፊ “ዋሽተው” መረጃ ስለሰጡኝ ነው,,,,,ሃቁ ግን 17 እስረኞች ከእሳቱ ለማምለጥ ሲሞክሩ እርስ በእርስ ተረጋግጠው ህይወታቸው አልፏል ይህንንም የአማራ ክልል ማረሚያ ቤቶች ኮሚሸን ኮሚሽነር አስተዳደር ሃላፊ በላይ ዘለቀ የሚባሉ (ስሙንማ ይዘውታል) ገልፀውልኛል ” ሲል ማምሻውን አስተባብሏል,,,,, (አላግጧል)

1ኛ, ብሔራዊ ቴሌቪዥናችን ያልተረጋገጠ መረጃ የሚያቀርብ ግድ የለሽ ተቋም መሆኑን አውቀናል
2ኛ, ማረሚያ ቤቶቻችን በስራቸው ላሉት ዜጎች ህይዎት እንኳን ግድ በሌላቸው ውሸታም አልያም በስራቸው ባለ ማረሚያ ቤት ስለሚከናወነው ነገር ምንም እውቀት በሌላቸው ሰዎች እንደሚመሩ አጋጣሚው ነግሮናል !!

17 ሰውኮ እጅግ ብዙ ነው,,,, የሃዘን ቀን ሁሉ በመላው ኢትዮጲያ መታወጅ ያለበት ጉዳይ ነው,,,,,17 ኢትዮጵያዊያን የሚያድናቸው አጥተው በማረሚያ ቤት ማለቃቸው ብሔራዊ ውርደት አቅመ ቢስነት ነው! ! በዚህ ላይ የጋዜጠኞቹ ወሽካታነትና ከህዝቡ ሃዘን በላይ ተቋሞቹ ለማይረባ ፖለቲካቸው ማሰብ ያሳፍራል! !

ጋዜጠኞች በተለይ በአል እና ድግስ በያለበት ለመገኘት ማንም የማይቀድመው የክልሉ ቴሌቪዥን በወቅቱ ከማንም በፊት በቦታው መገኘት እና ትክክለኛ መረጃ ማድረስ ነበረበት,,,, ቢሯቸው ተዘፍዝፈው በስልክ ሰው አልሞተም,,, ተሳስተን ነው ሙቷል እያሉ የሚዘላብዱት ምናይነት አሳፋሪ ሙያዊ ስነምግባር ቢኖራቸው ነው?

ደግሞ ኢቢሲ “ስህተቱ የአቶ እከሌ ነው እርማቱ የማንትስ ነው ” እያለ የሚቀልደው የመንደር እድር ወይም የቤተ ዘመድ ጉዳይ መሰለው እንዴ ?? ይሄ አንገብጋቢ የሆነ አገራዊ ጉዳይ ነው,,,, መንግስት እኔ እጠብቃቸዋለሁ ብሎ በራሱ ሃላፊነት ስር ያስቀመጣቸውን የህዝብ ልጆች መነሻው ምንም ይሁን ምን የሞታቸው ምክንያት እሳቱም ይሁን “እርግጫ ” ወይም ሌላ,,,, ብቻ ሃላፊነቱን ባለመወጣቱ 17 ወገኖቻችን ህይወታቸው አልፏል! !

ለሟች ወገኖች መፅናናትን እየተመኘሁ መንግስትም ሆነ በመንግስት ትዛዝ የምትንቀሳቀሱ የሚዲያ ተቋማት ይህን ጉዳይ በዘገባችሁበት ግዴለሽና አሳፋሪ አዘጋገብ ለእናተም ቤተሰብና ላቆሰላችሁት ኢትዮጲያዊ ሁሉ ፈጣሪ የሚያፅናና ቀን ያምጣ ከማለት ሌላ የምለው የለኝም! !


The post እናንተ እውነትን የምትደባብቁ ነግ በኔ በሉ! ! (አሌክስ አብርሃም) appeared first on EthioSun.