ዜና ጎንደርና ጎጃም – ነሐሴ 22 ቀን 2008 ዓ.ም #ግርማ_ካሳ

14067625_1231272990238114_999536353738257774_n

በጎጃም ከዳር እስከ ዳር ህዝባዊው እንቅቃሴ እየተቀጣጠለ ነው። ነሐሴ አንድ ቀን ጎንደርን ተከትሎ ባህር ዳር ከግማሽ ሚሊዮን ህዝብ በመውጣት አገሪቷ ከተነቃነቀች በኋላ በሶስት ሳምንታታ ብቻ ፣ የነጻነት ሰደድ እሳት ደብረ ማርቆስ፣ ፍኖተ ሰላም ፣ ደምባጫ፣ ግንደወይን ፣ ቡሬ እያለ ዛሬ ደግሞ የአገር ምድርን አጥለቅልቋል።፡ ዳንግላ፣ ኮሶበር፣ ዱርቤት የመሳሰሉ ከተሞች በሕዝብ ማእበል ተጥለቅልቀው ነው የዋሉት።

የአማራው ከልል የብዙ ብሄረሰቦች ክልል ነው። በዘር ሳይከፋፈሉ፣ ተከባብረው ለዘመናት በፍቅር የኖሩ። ምንም እንኳን ገዢው ፓርቲ ቅማንት፣ አገው፣ አማራ ፣ ትግሬ እያለ ለዘመናት በፍቅር የኖረን ህዝብ ለመከፋፈል ቢሞክር በአማራው ክልል ያለው ህዝብ፣ አማራው፣ አገዉን፣ ቅማንቱ ሁሉ ለዘረኛው የሕወሃት አገዛዝ ቀይ ካርድ እየሰጠ ነው። እኛ ኢትዮጵያዊያን ነን ፣ በዘር አንከፋፈልም እያለ ነው።

የቻግኒ፣ የዚገም፣ የአዘና፣ የአየሁ፣ የጃዊ ህዝብ ቀን ቆርጦ እምቢተኝነቱን እንደሚቀላቀሉ ታውቁአል።

እስከአሁን ባሉት መረጃዎች፣ ከአዲስ አበባ በደጀን ከዚያ በደብረ ወርቅ አደርጎ ወደ ባህር ዳር የሚወስደው መንገድ፣ ከአዲስ አበባ በደጀን ከዚያ በደብረ ማርቆስ፣ ደንበጫ አድርጎ ወደ ባህር ዳር የሚወሰደው መንገድ፣ ከወለጋ በቡሬ አድርጎ ወደ ባህር ዳር ደብረ ማርቆስ የሚወስደው መንገድ፣ ከቤኔሻንጉል በቻግኒ ፣ ዳንግላ አድርጎ ወደ ባህር ዳር የሚወስደው መንገድ፣ ከደሴ በምርጦ ለማሪያም በኩል አደርጎ ወደ ባህር ዳር የሚወሰደ መንገድ በሙሉ እየተዘጉ ነው።

በሰሜን እና ደቡብ ጎንደር ተቃዉሞው አሁንም እንደተቀጣጠለ ነው። ሐምሌ 5 ቀን የአምራር ተጋድሎ ተቃወሞ ከተጀመረ ጊዜ ሕዝባዊ ተቃዉሞዉን ያልተቀላቀለ የሰሜን እና የደቡብ ጎንደር ዞን ከተማም ሆነ ወረዳ አለ ብሎ ለመናገር አይቻልም።

ይህ አይነት የሕዝብ መነቃነቅ በአይነቱ የተለየ ከመሆኑን የተነሳ አብዛኛው የመከላከያ ሰራዊትና ፖሊስ ሃይልንም ማሰለፍ የቻለ የስለጠነና በብስለት የሚመራ እንቅስቃሴ እንደሆነ ከፍሬው ማየት ይቻላል።

ገዢው ፓርቲ አሁን የሕዝብን ጥያቄ ለማክበር ፍቃደኛ አልሆነም። ሕዝቡ ወልቃኡት የጎንደር ናት ብሎ ተቃዉሞ ቢያሰማም ገዢዎች የወልቃት ጉዳይ የሚፈታው በመቀሌ ነው የሚል ምላሽ በይፋ ሰጥተዋል። ለሕዝብ ጥያቄ ያላቸዉንም ንቀት ገልጸዋል።
ከፍተኛ የወታደር ሃይል በማሰማራት፣ የአማራ ክልል መንብስትን በማፍረስ፣ በቀጥላ ከአዲስ አበባ ሳይሆን ከመቀሌ የኮምናድ ሴንተር የአማራዉን ክልል ለማስተዳደርና ተቃዉሞዎችን ለመጨፍለቅ በሕወሃቶች ዘንድ ስምምነት እንደተደረሰም ይነገራል። በቅርቡም “ሰላም ማስጠበቅ አልቻላችሁ፣ በሙስና ተጨማልቃቹሃል” በሚል አቶ ገዱ አንድርጋቸውን ጨመሮ በርካታ የብአዴን አመራር አባላት ሊወገዱ እንደሚችሉም ተንታኞች ይናገራሉ።
አባይ በረሃ
——–

ከአዲስ አበባ ወደ ደብረ ማርቆስ በሚወስደው መንገድ ላይ የሚገኘውን የአባይ ድልድል ተዘግቷል።

14141629_1231273373571409_2096605112540034480_n

ቲሊሊ፣ አዲስ ቅዳም፣ አንከሻ
—————————

በቲሊሊ ከተማ የጨካኙ መለስ ዜናዊ ቢልቦርድ በአፍጢሙ ተደፍቷል።በአዲስ ቅዳም እና አንከሻም እንደዚሁም ህዝብ በነቂት ወጥቶ ለሕወሃት አገዛዝ ያለውን ጥላቻ ገልጿል።

ኮሶበር ከተማ
———–

አንድ ፎቅ ተሰባበሮ እቃውን አውጥተው አቃጥለዋል። ሰባት ሰው ሞቷል። በርካታ ዜጎንች ቆስለዋል። በኮሶበር 7 ሠዎች በነፍሠ በላው አጋዚ መገደላቸውን እና በርካታ ውጣቶች መቁሠላቸውን ማወቅ ችለናል። መከላከያ እና ፓሊስ ህዝባዊነቱን አሳይቷል። ከሞቱት ውስጥ አንድ የዞን አመራርም እንዳለበት ታውቁአል።

ዳንግላ
——

የዳንግላ ህዝብ በነቂስ ወጥቶ የአማራ ተጋድሎን ተቀላቅሏል። በአማራው ክልል የሚደረገው ተቃዉሞ የአማራ ተጋድሎ ብቻ ሳይሆን የአገዎችም በክልሉ የሚኖሩ ሌሎች ብሄረሰቦችም ተጋድሎ ነው። በዳንግላ 3 ዜጎች መቁሰላቸው ሲረጋገጥ የመተም ሰው ሊኖር እንደሚችል መረጃዎች ይጠቁማሉ።

ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክና ሌሎች ሁለት ባንኮች፣ አንባሻው ባለኮከቡ የወያኔ ባንዲራን በማውረድ ትክክለኛውን የአባቶቻችን ሰንደቅ አላማ ተሰቅሏል። ጀግኖቹ የአገው ልጆች «የአማራ ወንድሞቻችን ደም የኛም ደም»፤ «ወልቃይት የኛ ነው» ፤ «ጀግናችን ኮሎኔል ደመቀ በአስቸኳይ ይፈታልን» እያሉ መፈክሮች ሲያሰሙ ነበር።

ዱርቤቴ
——-

ሕዝቡ በዱርቤቴ ተነስቷል! ከእንግዲህ ለወያኔ አልገዛም ብሏል! በዱር ቤቴ የቅኝ ገዢው የወያኔ ባንዲራ ወርዶ የአባቶቻን ሰንደቅ አላማ ተሰቅሏል!

እንጅባራ
——–

በጎጃም አገው ምድር በእንጅባራ ከተማ ማ ሕዝቡ ከፍተኛ ተቃዉሞ አስመቷል። ሴት ወንድ ሳይል ነው ሕዝቡ በነቂስ የወጣው። እንዲህ አይነት በአገር መድር ታሪክ ታይቶ የማይታወቅ ነው። አስደናቂና የሚያኮራ ህዝባዊ እንቅስቅስቃሴ።

የቻግኒ፣ የዚገም፣ የአዘና፣ የአየሁ፣ የጃዊ ህዝብ ቀን ቆርጦ እምቢተኝነቱን እንደሚቀላቀሉ ታውቁአል።

ጎንደር
—–
በጎንደር የሥራ ማቆም አድማ ለአምስተኛ ቀን እየተደረገ ነው።
ደብረ ታቦር. አዲስ ዘመን ወሮታና ጋይንት
————————————–
በደቡብ ጎንደር ዞን ዋና ከተማ በሆነቸው በደብረ ታቦር ዛረ የተጀመረው የሥራ ማቆም አድማ በተሳካ ሁኔት ተከናዉኗል። ስራ ማቆም አድማ ነገም ይቀጥላል። በተመሳሳይ ሁኔያ በጋይንት፡ በወረታ በአዲስ ዘመን እንደዚሁም ንቅናቄው ተቀጣጥሏል።
ጋይንቶችም ወደ ደብረታቦር የሚወስደውን መንገድ ዘግተዋል፡፡ከባህርዳር ደብረታቦር ያለዉ መንገድም ወረታ ላይ ተዘግቷል፡፡ ደብረታቦር ህዝቡ ቤቱ ቁጭ ብሏል።የመኪናም ሆነ የባጃጅ እንቅስቃሴም የለም፡፡ ሱቆችም በሙሉ ዝግ ናቸዉ።

14088471_1231342283564518_1865075223122121069_n 14089312_1231342256897854_5290759135805204157_n
እስቴ
—-
በበየዳ በሰሜን ተራራቾ በታች በምትገኘው እስቴ የሥራ ማቆ አድማ ተደርጓል።

ዜና ጎንደርና ጎጃም – ነሐሴ 22 ቀን 2008 ዓ.ም #ግርማ_ካሳ