እነርሱ ሊገድሉት ፈልገውም በሕዝብ ትግል ግን ወንድማችን ይድናል – #ግርማ_ካሳ

14183726_203110083437411_406141083854654134_n

እነርሱም ሆነ ልጆቻቸው ትንሽ ጉንፋን በያዛቸው ቁጥር ከሕዝብ የዘረፉት ጎላር እየመነዘሩ፣ አሜኢርካን፣ አዉሮፓ፣ ታይላንድ ..እየሮጡ በመየሄዱ ነው የሚታከሙት። ሆኖም ግን ሌሎች ኢትዮያጵያዉን መሰረታዊ መብታቸው ተገፎ በአገራቸው በሰላምና በክብር መኖር አልቻሉም።

ሃብታሙ አያሌው የአንድነት ፓርቲ አመራር፣ አገሩን እና ሕዝቡን በመዉደዱ “ሽብርተኛ”ብለው ወደ ወህኒ ወሰዱት። ቶርቸር አደረጉት። ከቶርቸሩም የተነሳ ለሕመም ተዳረገ። ፍርድ ቤት ነጻ አለው። አቃቢ ሕግ ይግባኝ አለ። የይግባኝ ዉሳኔ ሳይሰጥ አመት ቆየ። ሕመሙ ጸናት። ተሰቃየ። በዉጭ አገር የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን ገንዘብ አሰባሰቡ፤ ወድ ዉጭ ሄዶ እንዲታከም። ዶክተሮች ሃብታሙ ዉጭ ሄዶ መታከም አለበት የሚል ደብዳቤ ጻፉ። ሆኖም ሕወሃቶች በቀለኞችና ቂመኞች ስለሆኑ ፣ ቅንጣት ያክል ርህራሄም ሆነ ሰብአዊነት የማይሰማቸው በመሆናቸው ይኸው አሁን ወደ ዉጭ ሄዶ እንዳይታከም አግደዉት ወንድማችን ለጥቂት ሳምንታት ከባባድ ማስታገሻ መድሃኒቶች ወስዶ መለስ ቢልለትም ፣ ብሶበት እንደገና ወደ ሆፒስትል ገብቷል።

ይህ ወንድም በህመምና በስቃይ ዉስጥም ሆኖ ግን ልቡና መንፈሱ አልተንበረከከም። አሁንም ነጻነትን እያወጀ ነው። ከአልጋ ላይ ሆኖ ዽምጹን እያሰማ ነው። ትላንት ሃባትሙ በመቶ ሺሆች መካከል ደርግም ወድቋል፣ ወያኔም ይወድቃል” እያለ ሲጮህ ነበር። ዛሬም ለብቻው ከቤተሰቦቹና ጥቂት ጓደኞቹ ጋር በአንዲት ክፍል በአልጋ ላይም ሆኖ የነጻነትን ድምጽ እያሰማ ነው። በህመምና በስቃይ ዉስጥም ሆኖም ወንድማችን ልቡና መንፈሱ አልተንበረከከም።አካሉን ቢጎዱትም መንፈሱን ግን ምንም ማድረግ እንዳልቻሉ እየነገራቸው ነው።

በጎጃም፣ በጎንደር፣ በወለጋ፣ ሃረረጌና በርካታ ቦታዎች ሕዝብ ተቃዉሞ እያሰማ ነው። እነ ሃብታሙ የተናገሩት እየሆነ ነው። የወያኔ አገዛዝ እየፈራረሰ ነው።

ሃብታሙ አያሌው በቅርቡ በወያኔዎች ፍቃድ ሳይሆን በህዝብ ትግል እና በ እግዚአብሄር እርዳታ ወደ ዉጭ ሄዶ ይታከማል። ከበሽታዉም ይድናል። በአዲስ አበባ ከተማ በመስቀል አደባባይ፣ በጎንደር፣ ደንበጫ፣ ፍኖት ሰላም፣ ደብረ ታቦርና እጅግ በጣም ብዙ ሌሎች ከተሞች እንደሆነው፣ የኢትዮጵያን ንጹኋን አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ባንዲራ ይዞ በሕዝብ ፊት በሙሉ ጤና ይቆማል !!!!

እነርሱ ሊገድሉት ፈልገውም በሕዝብ ትግል ግን ወንድማችን ይድናል – #ግርማ_ካሳ