የፖለቲካ እስረኞችና የሙስሊም መፍትሄ ኣፈላላጊ ኮሚቴ ኣባላት የሚገኙበት የቂሊንጦ ማጎሪያ ካምፕ የእሳት ኣደጋ ደረሰበት።

Image may contain: sky, outdoor and one or more people

የፖለቲካ እስረኞችና የሙስሊም መፍትሄ ኣፈላላጊ ኮሚቴ ኣባላት የሚገኙበት ከቂሊንጦ ማጎሪያ ካምፕ አካባቢ የተኩስ ድምፅ እየተሰማ ሲሆን እሳት ተነስቶ ጭስ እየታየ ነው። የአከባቢው ነዋሪዎች በተኩስ ጩኸት ተረብሸዋል።አካባቢው በወታደሮች ተከቡዋል። የእስረኞች ቤተሰቦችና ወዳጆች ወደ እስር ቤቱ እንዳይጠጉ ተደርጉዋል።በእስር ቤቱ ተኩስ የተጀመረው ሌሊት 9:00 ሲሆን እሳቱ የተነሳው ግን ጠዋት ነው።እስካሁን የቃጠሎውና የተኩሱ መንስዔ አልታወቀም። በሰው ላይ የደረሰ ጉዳት ስለመኖሩም ማወቅ አልተቻለም።

Source Article from http://www.mereja.com/amharic/511942

የፖለቲካ እስረኞችና የሙስሊም መፍትሄ ኣፈላላጊ ኮሚቴ ኣባላት የሚገኙበት የቂሊንጦ ማጎሪያ ካምፕ የእሳት ኣደጋ ደረሰበት።