አማራ ግብር አልከፍልም አለ!!!

የዐማራ ነጋዴዎች ግብር አንከፍልም ማለቱን አጠናክረው መቀጠል አለባቸው!!

no-taxes-480በጎንደር፣ በባህርዳር ፤ በደብረ ማርቆስ እና ተጋድሎው እየተስፋፋባቸው ባሉ አካበቢዎች ያሉ ነጋዴዎች ግብር አንከፍል አሉ፡፡
የመንግስት ባለስልጣናት የተጨማሪ እሴት ታክስ ለገቢዎች እና ጉምሩክ ባለስልጣን በየወሩ የገቢ ግብር ሪፖርት ማቅረብ የሚጠብቅባቸው ቢሆንም እስካሁን ላለፉት ሁለት ወራት የገቢ ግብር ያቀረበ ነጋዴ አልተገኝም፡፡

በአሁኑ ስዓት አገልግሎቶት ሰጭዎች ባቆሙበት ስርዓት የመንግስት ፋይናንስ ላለፉት ሁለት ወራት በጎንደር በዚህ ወር ደግሞ በባህር ዳር ያሉ ነጋዴዎች ከመንግስት አካላት ግብር እንዲከፍሉ ጥያቄ ቢቀርብላቸውም ለወንድሞቻችን ነፍስ መግደያ የጥይት መግዥ አናዋጣም፡፡ አሁን ላለው ስርዓትም እውቅና አንሰጥም ሲሉ ተናግረዋል፡፡
ላላፉት ሁለት ወራት ገቢዎች ምንም ግብር አልሰበሰበም!!

ሙሉቀን ተስፋው

አማራ ግብር አልከፍልም አለ!!!