ክርሰቲያኖ ሮናልዶ ከማንቺሰተር ዮናይትድ አጥቂዎች በታሪክ ዝቅተኛ ሀትሪክ የሰራ ተጫዋች መሆኑን ያውቃሉ?

l በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ  የምንግዜም ምርጥ 10  ኮከብ  ጎል አቆጣሪዎች ውስጥ ብቸኛ እንግሊዛዊ ያልሆነው ተጫዋችን ማን ነው? l እጅግ በጣም አሰገራሚ የፕሪሚየር ሊግ አጥቂዎችን ሪከርድ እንመልከት።

 

ትውሰታ በጨረፍታ l በቶማሰ ሰብሰቤ

በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ከአንድ እስከ አሰር የምንግዜም ኮከብ ጎል አሰቆጣሪዎች ሰም ዝርዝር ውስጥ አምሰተኛ ደረጃ  ላይ ብቻ እንግሊዛዊ ያልሆነ ተጫዋች ነው ያለው።ሌሎቹ ዘጠኝ ተጫዋቾች እንግሊዛዊ ናቸው።ፈረንሳዊው ሄነሪ ባሰቆጠራቸው 175 ጎሎች ብዛት አምሰተኛ የሊጉ የምንግዜም ጎል አሰቆጣሪ ነው።የቀድሞ የመድፈኞቹ ተጫዋችም እስካሁን ብቸኛ አሰር ውስጥ ሰሙ ያሰፈረ ተጫዋች ሲሆን ሺረር ፣ዋይኒ ሮኒ ፣አንዲ ኮል እና ላምፕርድ ከሄነሪ ፊትለፊት ከአንደኛ እሰከ አራተኛ ደረጃ ተቀምጠዋል።

ከመቶ በላይ ጎሎችን ያሰቆጠረው ብቸኛው አፍሪካዊ ተጫዋች ደሞ ዲዲየር ድሮግባ ነው።አይቮሪኮሰታዊው አጥቂ 104 ጎሎችን ለሰማያዊዎቹ አሰቆጥሯል።አዲባየር 97 ጎሎች በማሰቆጠር ሁለተኛ ነው።ፈረንሳይ እና ኔዘርላንድ ሁለት ሁለት ተጫዋቾቻቸው ከ100 በላይ ጎሎችን ያሰቆጠሩ ሀገራት ናቸው።ከፈረንሳይ ሄነሪ እና አኔልካ (125) ……ከኔዘርላንድ ጂሚ ፍሎይድ ሃሰንባንክ ( 127 ) እና ቫንፕርሲ (144 ) ጎሎች ናቸው።አለን ሺረር ለሁለት ክለቦች ና(ብላክበር እና ኒውካሰል) ከመቶ በላይ ጎሎች ያሰቆጠረ ብቸኛ ተጫዋች ነው።

ፍራንክ ላምፓርድ ከአማካኝ ተጫዋቾች ከፍተኛ ጎል አሰቆጣሪ ሲሆን ሪያን ጊጊስ በተሳተፈበት 21 የውድድር አመታት በእያንዳንዱ አመት ጎል ያሰቆጠረ የመጀመሪያው ተጫዋች ነው።በትንሽ ጫወታ 100 ጎሎችን በማሰቆጥ ሺረር ሲመራ ፣ኩን አጉየሮ በ147 ጨወታዎች 100 ጎሎችን በማሰቆጠር ሁለተኛ ነው።ከብራዚል  30 ጎሎችን ያሰቆጠረው ፊሊፕ ኮቲንሆ ከፍተኛ ጎል አሰቆጣሪ ነው።በ20 ጉሎች ኦሰካር ሁለተኛ ሲሆን በ17 ጎሎች ጄልቤርቶ ሲልቫ ፣ ራሜሬዝ እና ዊልያም ይከተላሉ።

አለን ሺረር እና ቫን ፕርሲ በሁለት የተለያዪ ክለቦች ኮከብ ተጫዋች ተብለዋል።ቴዲ ሺሪንጋ የመጀመሪያው የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የወርቅ ኳሰ በ1993 ያገኘ ተጫዋች ነው።አርሰናል እና ዮናይትድ አምሰት አምሰት ጊዜያት የወርቅ ጫማውን በተጫዋቾቻቸው በመውሰድ ይመራሉ።ኤሪክ ካንቶና የመጀመሪያውን ሶሰታ ወይም ሀትሪክ የሰራ ተጫዋች ሲሆን ላምፓርድ በ17 አመቱ ሶሰት ጊዜያት ሀትሪክ ሰርቷል።የቀድሞ የዮናይትድ ተጫዋች ኦሊገነር ሶልሻየር በ12 ደቂቃ ውስጥ 4 ጉሎችን ተቀይሮ ከገባ በሃላ አሰቆጥሯል።አዲባየር ደርቢ ካውንቲ ላይ በአንድ የወድድር አመት በደርሶ መልሰ ጫወታ ሀትሪክ የሰራ ብቸኛ ተጫዋች ነው።86 ጎሎችን ለማንቺስተር ያሰቆጠረው ሮናልዶ አንድ ጊዜ ብቻ ነው ሀትሪክ የሰራው በ2009።በሰድስት አመት ቆይታ ውስጥ ኒውካሰትል ላይ ብቻ ነው ያሰቆጠረው።

ሺንዥ ካጋዋ በ2013 ያሰቆጠረው ሀትሪክ የመጀመሪያው የእስያ አህጉር ተጫዋች በሊጉ ሶስታ ወይም ሀትሪክ ያስቆጠረ አድርጎታል።ሰዋሬዝ በኖርዊች ላይ ሶሰት ጊዜያት ሀትሪክ አለው።ሰይዶ ማኔ በሁለት ደቂቃ ከአምሳ ሰድሰት ሰከንድ ሀትሪክ በመሰራት የፈጣኑ ሀትሪክ ባለቤት ነው።ብዙ ሀትሪኮች በመሰራት ሸረር (11) ፣ፎለር (9) ፣ ሄነሪ (8) ናቸው።

በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የጎል ቁጥሮች ብዙ እውነታዎች አሉ።እጅግ አሰገራሚ ጎሎች ያየንበት ሊግ ምርጥ ታሪኮች እልፍ ቢሆኑም እኔ ዛሬ እነዚህን አሰታወሰኩ እናተ የምታሰታውሱትን በአሰተያየት መሰጫው አሰቀምጡልኝ።

 

 

The post ክርሰቲያኖ ሮናልዶ ከማንቺሰተር ዮናይትድ አጥቂዎች በታሪክ ዝቅተኛ ሀትሪክ የሰራ ተጫዋች መሆኑን ያውቃሉ? appeared first on ሳተናው: Ethiopian Amharic News | Breaking News 24/7: Your right to know!.

ክርሰቲያኖ ሮናልዶ ከማንቺሰተር ዮናይትድ አጥቂዎች በታሪክ ዝቅተኛ ሀትሪክ የሰራ ተጫዋች መሆኑን ያውቃሉ?