በስያትል ከተማ የተካሄደው የኢትዮጵያ አገራዊ አንድነት ጉባዔና እድምታው – ክፍል ሦስት (ታምራት ይገዙ)

 አሜሪካ ያላቹሁ ጠላ ቅመሱ
አፍሪካም ያላቹሁ ጠላ ቅመሱ
እንድ ሻላቃ ዳዊት እንድትጠነስሱ
አውሮፓ ያላቹሁ ጠላ ቅመሱ
ኢሲያና አውስትራሊያም ያላቹሁ ኑ ጠላ ቅመ
እንደ መምህሩ እንደ ጌታቸውም  እንድትጠነስሱ”

ሻለቃ ዳዊት /ጊዮርጊስ በስያትል ከተማ በተካሄደው የኢትዮጵያ አገራዊ አንድነት ጉባዔ ላይ እንዲህ ሲሉ ተደምጠዋል 

 

ተቃዋሚ ሃይሉፉከራእናጉራ ብቻነው ዝግጅት የለም ብለዋል::”

በመቀጠልም!

ተቃዋሚው እርስበርሱ ተነጋግሮ አያውቅም የጋራ አጀንዳም የለውም ነገ ደረስኩ ከነገ ወዲያ ደረስኩ እያሉ መፎከር ብቻ ነው ያለው ኢትዮጵያ ያለው ህዝብ ማንም ሳያደራጀው ቁጣው በገነፈለበት ወቅት አንድ ነገር ማድረግ ቢቻል ኖሮ ወያኔ ሊወድቅ ይችል ነበር። ግን በውጭ ያለው ከማጨብጨብና በኢሳት በኩል መረጃ ከማስተላለፍ በስተቀር ምንም ያደረገው ነገር የለም ይህ ውድቀታችን ነው።

በማስከተልም !

“መሰዋትነትን በጠቅላላው የከፈለው የኢትዮጵያ ህዝብ ነው ማንም ሳያደራጀው: በጎንደር; በጎጃም; በደቡብ; ባጠቃላይ በመላው አገር: ህዝቡ ተነስቶ ተቆጥቶ እና ቁጣው ገንፍሎ ወያኔን ባርበደበት ጊዜ ህዝቡን አስተባብሮ ደግፎ አንድ ነገር ማድረግ ቢቻል ኖሮ በእውነቱ ወያኔ ሊወድቅ ይችል ነበር   ለዚህ መጠየቅ ያለበት በዊጪ የሚኖረው ኢትዮጵያዊ (ዲያስፖራው)ነው::  አገር ቤት ውስጥ ያለው ህዝብ አስተባባሪ ሃይል አደራጅቶ ትግሉን ማስተባበር የማይችልበት ነገር ውስጥ ነበር የነበረው::  ስለዚህ ይህንን ማድረግ የሚችለው በውጪ ነው; ሀላፊነቱም በውጪ  በሚኖረው ኢትዮጵያዊ (በዲያስፖራው)ነው  ሃላፊነቱም በዲያስፖራው ውስጥ ያሉት የተቃዋሚ ሀይሎች ነበር:: እነሱ መነጋገር አልቻሉም ያን ግዜ ነው ይህንን ስንገነዘብ አገራዊ ንቅናቄ እንዲቆቆም ፕ/ር ጌታቸው እና እኔ እንሼት አድርገን ንግግሩን የጀመርነው::”

ሲቀጥሉ

“አገር ውስጥ አንድ ፌንዳል ሜንታል እንነስ ብንል አናሳ ቤሄረሰቦች ሁልግዜም ከኢትዮጵያ ጋር ምንም ችግር የለባቸውም የነሱ ችግር የዲሞክራሳዊ እና የመፍት ጥያቄ ነው::  ከኢትዮጵያዊነት ጋር ችግር እና ግጭት የነበረው የኦሮሞ ነፃ አውጪ ግንባር እና ባለመደራጀቱ አማራው ነበር::   የኦሮሞ ነፃ አውጪ ግንባር ትልቅ ባህር አቆርጦ በኢትዮጵያዊነት አምኖ ኦሮሞ ዲሞክራት ፍሮንት ብሎ ሲመጣና  ምን ውስጥ ልግባ ሲል የተደራጀ የአማራ ሀይል የለም በእናሱም እምነት በእኛም እምነት:: “

ይህንን የሻለቃ ዳዊት ልብ የሚመስጥ ንግግር ያዳመጠ ሁሉ ተመሳሳይ ጥያቄ የሚያቀርብ ይመስለኛል እኔም  እንዴት ነው አፋሩ ተደራጅቶል; ሲዳማው ተደራጅቶልከኢትዮጵያዊነት ጋር ችግር እና ግጭት የነበረው የኦሮሞ ነፃ አውጪ ግንባር የኦሮሞ ዲሞክራት ፍሮንት በማለት ተደራጅቶል ብለው ሲናገሩ አማራው ግን አልተደራጀም ሲሉ ምን ዓይነት መመዛኛ አስቀምጠው ነው ያመራውን አለመደራጀት አበክረው የተናገሩት የሚል ጥያቄ ጭሮብኝ አልፎልአማራው ከኦሮሞ ዲሞክራት ፍሮንት ባላነሰ  ተደራጅቶልከአፋሩ እና ከሲዳማው በተሻለ ተደራጅቶል የሚል ሃሳብ አለኝ  ምክንያቱም በተለያዩ የአሜሪካ ከተሞች ስብሰባዎችን እየጠሩ ይደግፈናል ያሉትን የህብረተሰብ ክፍል አወያይተዋል  ከመደራጀት አልፈው የመገናኛም ጣቢያ ያላቸው አሉ ይህንን ደሞ እንደ ማንኛውም ሰው ተከታትየዋልው እየተከታተልኩትም ነው ::  ምናልባት የሻለቃ ዳዊት መልስ ወይም አስተያየት  ሊሆን የሚችለው አማራው ከመደራጀት አልፎ በቁጥር ስለበረከቱ አንዱን አቅርበን ሌላውን ላለማራቅና ክፍፍል በመሃላቸው ላለመፍጠር ስንል የኢትዮጵያ አገራዊ ንቅናቄ ሲመሰረት አልጠራናቸውም የሚል መልእክት ቢተላለፍ አንኮን ያስኬዳል ካዛ ባለፈ ግን አማራው አልተደራጀም ሲባል ሌሎች ጥያቄዎች ያስነሳል ለምሳሌ ህወሐት ኢህዴንን በእንጀራ አባትነት አሳድጎ ብአዴንን እንድ ሳሙና ለራሱ እንዲመች አድርጎ እንደፈጠረውደኢህዴንና ኦህዴድን በራሱ ልክ እንደሰራቸው ሁሉ ምናልባት እናንተ ደሞ አማራውን ለግንቦት ሰባትም እንዲመች አድርጋችሁ ጠፍጥፋችሁ ወደ ፊት ለመፍጠር አስባችሁ ይሆን?ከሆነ የአማራው ህዝብ ይህንንማ አታደርጉብንም  ” እናንተ ቤት የዋልወ የፖለቲካ ብልጥነት እኛ ቤት አምሽቶልብሎ መልስ የሚሰጣችሁ  ይመስለኛል ::  በሌላ በኩል ይህ የአውራ ድርጅት የማውጣት ትንቅንቅ የሚያስታውሰን አንድ ወቅት ላይ / መራራ ጉዲናህወሀት ደርግ የሰራውን ስህተት በፊልም እያየ የሚደግም ይመስላልብለውን ነበር  አሁንስ የምናየው የግንቦት ሰባትን አውራ ድርጅት አድርጎ የማሰብ ጉዞ ህወህት የሰራውን ስህተት ህዝብ ረስቶታል ተብሎ ለመድገም የታሰበ ይሆን?:: 

በተጨማሪ ሻለቃ ዳዊት ከተለያዩ የመገናኛ ቡዙሀን ጋር ስለ አገራዊ ንቅናቄው በተመለከተ በጥያቄና መልስ ማብራሪያ ሲሰጡ ተደምጠዋል አብዛኛው የሚዲያ አውታሮች ከጠየቁት ጥያቄ ውስጥ

 1 በአገር ጉዳይ ላይ ያገባኛል የሚሉት በርካቶች ናቸው ሁሉንም ድርጅቶች በአገራዊ ንቅናቄ ውስጥ ለማካተት ተሞክሮል ወይለሚለው ጥያቄ ለአዲስ ዽምጽ ጋዜጠኛ; ለህብር ሬዲዮ እና ለአማራው ድምጽ ሬዲዮ አቅራቢዎች  የሰጡት መልስ እርስ በእርሱ ይቃረናል እንዱ የሰጡትን መልስ ሌላው አይደግሙትም::   ይህ የሚያሳየው በእኔ አስተያየት የአገር አድን ንቅናቄ ስሙ እንጂ ያስፈለጋችሁ ስሙ የያዘውን ሀላፊነት አይደለም:: 

2 እነዚህ አራት ድርጅቶች በምን መመዘኛ ተመረጡ ሲባሉ የሰጦቸው መልስእነዚህ አራት ድርጅቶች የተመረጡት ኢትዮጵያ ውስጥ ሜዳ ላይ ትግል የሚያካሂዱ በሞሆናቸው ነው ያሉት::”  የኔ ጥያቄ ለተከበሩn ሻለቃ ዳዊ የትኛው ድርጅት ነው ሜዳ ላይ ያለው? የሲዳማው? የኦሮሞ ዲሞክራት ፍሮንት? የአፋሩ ወይስ የግንቦት ሰባት እባኮሆን በእውነተኝነትና በቅንነት መልሱልኝ? በሌላ በኩል ደሞ እነዚህ ድርጅቶች አገር ቤት ውስጥ ሜዳ ላይ ካሉ በንግግሮት መጀመሪያተቃዋሚ ሃይሉፉከራእናጉራ ብቻነው ዝግጅት የለም   ብለዋል”  ይህ አባባሎት እርስ በእርሱ አይጋጭም ወይ?::  እርግጥ ነው ግንቦት ሰባት ከፍተኛ አመራሮች  የኦሮሞ ውንድሞቻችንና እህቶቻችን በአዲስ አበባና አካባቢዋ በሰላማዊ መንገድ ከህወሀት ጋር ግብግብ በፈጠሩ ግዜ ባላቸው ሚዲያ ተጠቅመው አይዞችሁ መሃላችሁ ነን ሲሉ እንደነበር ይታወሳል::   የኦሮሞ

 

ውንድሞቻችንና እህቶቻችን በአዲስ አበባና አካባቢዋ በሰላማዊ መንገድ ከህወሀት ጋር ያደርጉትን ሰላማዊ ትግል ጋብ ሲልና በአማራው ክፍል በጎንደር እና በጎጃም የኦሮሞው ደም ደማች ነው ብለው ሰላማዊ ትግሉንና ሲያቀጣጥሉትና  ለህወሀት አንገዛም ብለው ሲነሱም አሁንም  ግንቦት ሰባት ባላቸው ሚዲያ ተጠቅመው አይዞችሁ መሃላችሁ ነን ሲሉ እንደ ነበር ሁሉም የሚያስታውሰው ነው :: በእኔ በኩል ይህንን የተመለከትኩት በሁለት መንገድ ነው እሱም 1ኛው ግንቦት ሰባት መንፈስ ነኝ ብሎ ህዝቡን ለማሳመን እየሞከረ እንደነበር ያሳያል     2ኛው ደሞ እናቶቻችን እንደሚሉትበጨው ደንደስ በርበሬ ተወደስየሚባለውን አገራዊ አባባል  ህዝብ አያውቀውም በማለት የታሰበ ይመስላል: ይህ በሌሉበት ቦታ አለን ብለው የተጫወቱት ፕሮፖጋንዳ ምን ያህል እንደሰራላቸው እራሳቸውን ይገምግሙ::  ከዛ ዊጪ ከአራትና ከአምስት ግዜ በላይ በኤርትራ የወታደራዊ ሃይል አስመረጥኩ ያለ ተዋጊ ድርጅት በዚሁሉ አጋጣሚ አንኮን የበሬ ግንባር የምታክል መሬት ከኢሀድግ ነጥቆና ተቆጣጥሮ አላሳየንም:: ይህንን ስመለከት በወጪ አገር ያሉ ድርጅቶች  ወይም ተቃዋሚ ሃይሉ እርሶ ሻለቃ ዳዊት እንደተናገሩት  “ፉከራእናጉራ ብቻነው የሚለውን ሙሉ በሙሉ እጋራለሁ  ሁሉም ያላቸው አቅም  እኩል ነው የሚል እምነት አለኝ:: 

ይህንን ካልኩኝ ዘንዳ አርሶም ሆኑ / ጌታቸው በጋሻው በሆደ ሰፊነት በአርቆ አስተዋይነት ከሁሉ በላይ ደሞ በአገራችን በኢትዮጵያና በውስጦ በሚኖሩት በመቶ ሚሊዮን ህዝብ ለይ ከፍ ሲል ላለፉት  አመታት ዝቅ ሲል ደሞ ለሃያ ስድስት ዓምት የደረሰውን ግፍና መከራ ግምት ወስጥ በማስገባት  በዊጪ አገር ያሉትን የአገራችን የኢትዮጵያ ጉዳይ ያገባናል የሚሉትን ድርጅቶች ጥርታችሁ እኛ የኢትዮጵያ አገራዊ ንቅናቄ እንዲፈጠር መንገድ አመቻችተናል እናንተ ምን ትላላችሁ ብላችሁ ሶስት ዋና ጉዳዮች ያላችሁትን ማለትም  1 ኢትዮጵያ የምትባል አገር አለች ብሎ የሚያምን 2 ሁለንተናዊ ዲሞክራሳዊ መፍቶች ይከበራሉ ብሎ የሚያምን 3 የስልጣን ምንጩ የሚሆነው በማንኛውም በምንግስት ደረጃ በህዝብ ምርጫ ነው ብሎ የሚያምን የሚለውን ለተስበሳቢው ስጥቶ እንዲወያይበት ማድረግና እነዚህን ሶስት ነጥቦች የሚያሞሉ አብረው ይሰራሉ የማያሞሉ ከሉ እራሳቸውን ከንቅናቄው ያገላሉ ማለት ነው::  ይህንን ብታደርጉ ኖሮ አሁን እናንተ የምትጠየቁትን ጥያቄ የሚጠየቁት እነዛን ሶስት መመዘኛ ሳያሞሉ ቀርተው የወጡት ድርጅቶች ነበሩ የሚል እምነት አለኝ:: 

እናንተንም እንደ እድሚያችሁና  እንደ እውቀታችሁ ላበረከታችሁት ከፍተኛ አስተዋጻ የተወሰነው የድርጅት ክፍል ብቻ ሳይሆን አብዛኛው ድርጅትና ከድርጅት ውጪ ያለው ኢትዮጵያዊ ሁሉ   ጥንስሣችሁ በሆደ ሰፊነት; በአርቆ አስተዋይነትና በገለልተኝነት የተጠነሰስ ጥንስሥ ነው ብሎ  ሁሉም የድርሻውን ይወጣ እንደነበረ እርግጠኛ ሆኜ ብናገር የተሳሳትኩ አይመስለኝም ምክንያቱም 99 ፐርሰንቱ ኢትዮጵያዊ ህወሀት ስልጣኑን ለኢትዮጵያ ህዝብ እንዲያስረክብ ይፈልጋል የጠፋው ይህ እውን እንዲሆን በሆደ ሰፊነት; በአርቆ አስተዋይነትና በገለልተኝነት ተነሳስቶ ላለፈው ሰላሳና አርባ አመት በተለይ ትውልድ ብለን በምንጠራቸው ወንድሞቻችና እህቶቻችን ውስጥ ያለውን እኛ እና እነሱ የሚለውን በድርጅቶች ውስጥ ያለውን  ሹኩቻ በቅንነት የሚፈታ ቅን ሰው ነው ያለገኘነው በመሆኑም ትግሉ ከሕወሓት ጋር ሳይሆን የጎንዮሽ ሆነ::  በሌላ በኩል እርግጠኛ ሆኜ የምናገረው የችግር አፈታት እውቀቱና ተመክሮ ያላቸው አንጋፋ ሙህራንና ወጣት ሙህራኖች በብዛት አሉን እነሱ ግን የሚሰራውን እያዩና እየሰሙ መቼ ነው ሁላችንም ከስህተታችን የምንማረው ወንድሞቻችን ምን ነካቸው በማለት አርፈው መቀመጥን መርጠዋል የሚል እምነትም አለኝ:: 

ይህን የምልበት ምክንያት ቢያንስ ላለፉት አርባ አመታት የተሄደበት መንገድ ትክክል ሳይሆን በመቅረቱ አገራችን ኢትዮጵያ ከድጡ ወደ ማጡ በመግባት ላይ ባለችበት በአሁኑ ሰዓት አሁንም እንደ አለፉት አመታቶች አገርን ለማዳን አንዱን ድርጅት ማቅረብ ሌላውን ድርጅት ማራቅ በእውቀት ከከበረና የህይወት ተመክሮ ካለው ማንኛውም ኢትዮጵያዊ አይጠበቅም ባይሆን የሀገራችንን ህዝብ ከህወሀት መጥፎ አገዛዝ ለማላቀቅ  እንደ እኩያ ወንድምና እንደ እኩያ እህት አንት ትሻል  አንቺ ትሻይ ተባብሎ የከረረውን አላልቶ የተራረቀውን አቀራርቦ  በዊጪ ያለውን የሰው ሀይል መጠቀም ይቻል ነበር ይህ ግን ሲሆን እየታየ አይደለም::  እንደ እውነቱ ከሆነ ተላላቅ ወንድሞቻችን በትምህርት የቀመሳችሁትን እውቀት ካላችሁ የእድሜ ተመክሮ ጋር በማዋሀድ በዛ ላይ ደሞ ቅንነትን በመጨመር አገራዊ ንቅናቄውን ብትጠነሰሱት ኖሮ በዊጪ አገር እየኖረ የአገሩ ጉዳይ እንደ ፍም እሳት ለሚለበልበው ኢትዮጵያዊ ሁሉ ዘመኑን የዋጀ አንድ የመታገያ በር ከፈታችሁለት ይባል ነበር   ይህን ከመስራት ይልቅ  ከእንደኔ ካለው ተራ ግለሰብ የማይጠበቅና አባቶቻችን እንደሚሉትየእብድ ገላጋይ ዱላ ያቀብላልአሊያም እናቶቻችን እንደሚሉትየበላችው ያገሳታል በላይ በላዩ ያጎርሳታልየሚመስል ዘይቤ ተይዞ ሌላ አውራ ድርጅት ለማውጣት ስንቦዝን እድሚያችንን ፈጀነው::  ከእንደዚህ አይነት የመጥፎ የፖለቲካ አስተላለፍ እራሳችንን የምናቅበውና የመቻቻል ፖለቲካ ቅብብሎሽና በአገራችን የዲሞክራሲ ሀሁ መቼ ነው የምንጀምረው? ይህንን ሁሉም ኢትዮጵያዊ በልበ ቅንነት ሊያስበውና ሳይፈራራ ሊነጋገርበት  ይገባል እላለው::

በመጨረሻም

የተከበሩ ሻለቃ ዳዊት ወ/ጊ   በአንድ ወቅት  ላይ ሰለ ሩዋንዳ የዘር ፍጅት ምክንያቶችና ለኢትዮጵያውያን ስለሚሰጠው ትምህርት በሚል ጥናታዊ ጽሁፎት ላይ በመግቢያው ላይ ይህን ብለው ነበር

The Case of Rwanda:  Lessons for Ethiopia.

“This is article is meant for Ethiopians to remind them to learn lessons from the Rwandan genocide. Some might think that such kind of scenario will never happen in Ethiopia. But just think about it: who thought that a country called Somalia with one language, one ethnic group and one religion would so rapidly fall apart and be a failed state for two decades? Who would have thought that the former Yugoslavia would disintegrate and result in the kind of genocide and ethnic cleaning we have seen in the heart of Europe, sending many leaders to the international criminal court? Who would have thought that South Sudan, which had its independence in 2011, after decades of war, would descend to a civil war that is causing the death and displacement of hundreds of thousands of South Sudanese? Who would have thought that Muammar Gadhafi would be overthrown in such a swift and brutal way and the country plunging into civil war and becoming the breeding ground of terrorists like ISIS, an evil that slaughtered many innocent young Ethiopian migrants?  And the list can go on.”

እንደዚ አይነት ሁሉንም ያካተተ ጥናታዊ ጽሁፍ ለንባብ ያቀረብና የአገሩን ጉዳይ ብቻ ሳይሆን በአጠቃላይ የአፍሪካን የዘመኑን ችግር የዳሰሰ እውቅ ሙህር እንዴት ነው አገራችን ኢትዮጵያ በችግር አፋፍ ላይ እያለች ያንን ችግር የሚፈቱት በግንቦት ሰባት ፊት አውራሪነት; በኦሮሞ ዲሞክራት ፍሮንት; በአፋር ህዝብድርጅት እና በሲዳማው ህዝብ ድርጅት ጋሻ ግሬነት ህወሀት ላለፉት ሃያ አምስት አመታት የተበተበው ቆጠሮው ይፍታል ብሎ በማሰብ የኢትዮጵያ አገራዊ ንቅናቄን ስትመሰርቱ እነዚህን ድርጅቶች ብቻ ጠርታችሁ በሉ አገራዊ ንቅናቄውን መስርቱ ያላችሁት? በእኔ እምነትይህንን ባሉበት ሰዓት  ያ ሁሉ የደከሙበት ጥናታዊ ጽሁፍ  ውሃ በላው ማለት ነው::   በሌላ በኩል ጥናታዊ ጹሁፎትን ላነበበ ኢትዮጵያዊ ሁሉ  የማይፈታ እንቆቅልሽ ጥለውበት እንዳለፉ እገምታልው ምክንያቱም ያለውን ችግር በተወሰነ ደረጃ ቢሆን እንኮን ይፈታል ተብሎ የተቀመጠው መፍትሄ ሃሳብ እነዚህ ድርጅቶች ባቻ በመሆናቸው ችግሩና መፍትሄው በፍጹም አይመጣጠንም ባይ ነኝ::  እርሶስ  ምን ይመስሎታል በአሁን ሰአት ላይ ሆነው ሲመለከቱት?::

በሌላ በኩል እርሶም ሆኑ ፕ/ር ጌታቸው በተላያዩ ሚዲያዎችላይ ስለ አገራዊ ንቅናቄው ገላጻ ስትሰጡ እኛ እንሸቲቭ አድርገነ ይህንን አገራዊ ንቅናቄ እንዲቆቆም ጥረት አድርገናል ከአሁን ቦሃላ ሌሎች ድርጅቶች ሊቀላቀሎቸው ይችላሉ ስትሉ ተደምጣችዋል ይህ አበባል እንዳያማህ ጥራው እንዳይበላ ግፋው አያስመስልባችሁም ወይ?”

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

………………………

በስያትል ከተማ የተካሄደው የኢትዮጵያ አገራዊ አንድነት ጉባዔና እድምታው – ክፍል ሦስት (ታምራት ይገዙ)